EUR/USD1.0842GBP/USD1.2718XAU/USD4,148BTC/USD85,252USD/JPY151.32USD/ETB57.8500AUD/USD0.6512EUR/USD1.0842GBP/USD1.2718XAU/USD4,148BTC/USD85,252USD/JPY151.32USD/ETB57.8500AUD/USD0.6512
🏛️ NegadRas Academy — building the foundation, one brick at a time.📰 Fed signals rate decision this week — expect volatility in USD pairs📰 Gold holds near record highs as safe-haven demand rises📰 ECB inflation report due Thursday — EUR traders brace for impact🏛️ NegadRas Academy — building the foundation, one brick at a time.📰 Fed signals rate decision this week — expect volatility in USD pairs📰 Gold holds near record highs as safe-haven demand rises📰 ECB inflation report due Thursday — EUR traders brace for impact
TRADING PSYCHOLOGY

November 15, 2026

3 min read

ከመጽሐፍ ገጾች | ክፍል ፫ The Alchemist (በፓውሎ ኮኤሎ)

👑 ነጋድራስ  መሳፍንትBy 👑 ነጋድራስ መሳፍንት🛡️

ከመጽሐፍ ገጾች | ክፍል ፫   The Alchemist (በፓውሎ ኮኤሎ)

​📚 ከመጽሐፍ ገጾች | ክፍል ፪

​የሳምንቱ መጽሐፍ፦The Alchemist (አልኬሚስቱ) (በ Paulo Coelho)

የትኩረት ነጥብ፦ የእረኛው ሳንቲያጎ ጉዞ፣ የክሪስታል ነጋዴው ምክር እና እውነተኛው የትሬደሩ "ውድ ሀብት"! ​

ቤተሰብ👋

በዚህ ሳምንት "ከመጽሐፍ ገጾች" ዓምዳችን፣ከቀጥተኛ የትሬዲንግ መጽሐፍት ትንሽ ወጣ ብለን፣ ዓለምን ካነቃቁ ድንቅ የፍልስፍና እና የስነ-ጽሑፍ ስራዎች መካከል አንዱን ይዘን ቀርበናል። ብዙ ጊዜ ስለ ትሬዲንግ ስናስብ አእምሯችን የሚሄደው ወደ ቻርት፣ ኢንዲኬተር እና ኢኮኖሚያዊ ዜናዎች ብቻ ነው። ነገር ግን ትሬዲንግ በመሰረቱ የሰው ልጅ የራሱን ማንነት፣ ፍርሃቱን እና ሕልሙን የሚፈትንበት ጥልቅ የሕይወት ጉዞ ነው። ለዚህም ነው የፓውሎ ኮኤሎ (Paulo Coelho) The Alchemist የተሰኘው መጽሐፍ፣ ስለ ቻርት አንድም ቃል ሳይናገር፣ ስለ ትሬደሮች የሕይወትና የስነ-ልቦና ጉዞ ግን ፍጹም በሆነ መንገድ የሚተርከው!

መጽሐፉ የሚያጠነጥነው ሳንቲያጎ በተባለ አንድ ወጣት እረኛ ዙሪያ ነው። ሳንቲያጎ በግብፅ ፒራሚዶች ስር የተቀበረ አንድ ትልቅ ውድ ሀብት እንዳለ በተደጋጋሚ ሕልም ያያል። ይህንን "የሕይወት ጥሪውን" (Personal Legend) ለማሳካት የለመደውን ምቹ ሕይወትና በጎቹን ትቶ ወደማያውቀው የሰሃራ በረሃ ረጅምና አድካሚ ጉዞ ይጀምራል። በጉዞው መጀመሪያ ላይ ግን ያልጠበቀው ነገር ይገጥመዋል፤ ያለውን ገንዘብ ሁሉ በሌቦች ይዘረፋል! ተስፋ ቆርጦ በባዶ እጁ በቀረበት ሰዓት፣ አንድ የመስታወትና የክሪስታል እቃዎች ነጋዴ ጋር ተቀጥሮ መስራት ይጀምራል። እዚያ ሱቅ ውስጥ ሳንቲያጎ የተማረው ትምህርትና በበረሃው ያሳለፈው ፈተና፣ እያንዳንዱ ትሬደር ከጀማሪነት ወደ ብስለት በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ የሚያልፍበት ፍጹም ነጸብራቅ ነው።

ከዚህ ድንቅ የፍልስፍና መጽሐፍ ውስጥ ለትሬዲንግና ለሕይወታችን የምንቀዳቸው ዋና ዋና ጥበቦች የሚከተሉት ናቸው፦

1.​የጀማሪው እድል እና የበረሃው ፈተና፦ ፓውሎ ኮኤሎ በመጽሐፉ ውስጥ "ማንኛውም ሰው አዲስ ጉዞ ሲጀምር፣ መንፈሱ እንዲበረታ መጀመሪያ ላይ 'የጀማሪ እድል' ይሰጠዋል" ይላል። ወደ ትሬዲንግ ስንገባም ብዙዎቻችን ያለ ምንም እውቀት በዴሞ ወይም በትንሽ አካውንት ጥሩ ትርፍ ሰርተን እናውቃለን። ይህ ግን ወደ በረሃው መሳቢያ እንጂ እውነተኛ ብቃት አይደለም። ልክ ሳንቲያጎ ገንዘቡን እንደተዘረፈው፣ ትሬደሩም የመጀመሪያውን ከባድ ኪሳራ (Account Blow) ሲያስተናግድ እውነተኛው የትሬዲንግ ትምህርት ይጀምራል። በዚያ ቅጽበት ተስፋ ቆርጦ የሚመለስ ሰው ውድ ሀብቱን መቼም አያገኘውም፤ ከውድቀቱ ተምሮ እንደ ሳንቲያጎ እንደገና ከዜሮ መገንባት የሚጀምር ግን ለስኬት ይታጫል።

2.የክሪስታል ነጋዴው እና የለውጥ ፍርሃት፦ ሳንቲያጎ ተቀጥሮ ይሰራበት የነበረው የክሪስታል ነጋዴ፣ ለዘመናት አንድ ምኞት ነበረው፤ ነገር ግን ምኞቱን ለማሳካት የሚጠይቀውን ለውጥና ሪስክ ስለሚፈራ በለመደው ትንሽ ሱቅ ውስጥ እድሜውን ጨረሰ። በትሬዲንግም ብዙ ሰዎች ትልቅ ትርፍና ነፃነት ይመኛሉ፤ ነገር ግን አዲስ ዲሲፕሊን መለማመድ፣ ስህተታቸውን መቀበል እና ከለመዱት የስሜታዊነት ባህሪ መውጣት ይፈራሉ። የክሪስታል እቃዎች በጣም ስስ እንደሆኑና ጥንቃቄ እንደሚሹ ሁሉ፣ የትሬዲንግ ካፒታልህም እጅግ ስስ ነው፤ በጥንቃቄና በዕቅድ ካልያዝከው በአንድ ቅጽበት ታጥዋለህ።

3.የገበያውን ቋንቋ መረዳት (Reading the Omens)፦ ሳንቲያጎ በበረሃው ውስጥ መንገዱን ያገኘው የተፈጥሮን ምልክቶች፣ የነፋሱን አቅጣጫ እና የበረሃውን ቋንቋ ማንበብ ሲችል ነበር። በቻርት ላይም ገበያው በየሰዓቱ በካንድሎች፣ በዋጋ እንቅስቃሴ (Price Action) እና በጊዜ ዑደቶች አማካኝነት ያናግረናል። ነገር ግን የራሳችንን ስሜትና ፍላጎት እያዳመጥን ከሆነ፣ የገበያውን ቋንቋ መስማት አንችልም። ውስጣችን ሲረጋጋ ብቻ ነው ገበያው የሚሰጠንን ምልክቶች (Confluences) በጥራት ማንበብ የምንችለው።

4.​ውድ ሀብቱ ያለው ጉዞው ውስጥ ነው (The Alchemist’s Secret)፦ አልኬሚስቶች እርሳስን (Lead) ወደ ወርቅ የመቀየር ጥበብ ያላቸው ጠቢባን ናቸው። በትሬዲንግ ውስጥም እውነተኛው አልኬሚስት አንተ ነህ! ትኩስ፣ ስሜታዊ እና ችኩል የሆነውን ማንነትህን (እርሳሱን)፤ በዲሲፕሊን፣ በትዕግስት እና በልምድ አቅልጠህ ወደ ፕሮፌሽናል ትሬደርነት (ወደ ወርቅ) ትቀይረዋለህ። ሳንቲያጎ በመጨረሻው ፒራሚዱ ስር ደርሶ ውድ ሀብቱን ሲያገኝ የተረዳው ትልቁ ምስጢር አለ፤ "ከዚያ ወርቅ በላይ ዋጋ ያለው፣ ያንን ወርቅ ለማግኘት ሲል በበረሃው ውስጥ የገነባው ጥንካሬ፣ ጥበብ እና የጸና ማንነት ነው!"

ቤተሰብ፣ እኛም በትሬዲንግ ውስጥ የምንፈልገው የፋይናንስ ነፃነትና የፕሮፕ ፈርም ፈንድድ አካውንት እዚያ ፒራሚዱ ስር የተቀበረው ወርቅ ነው። ነገር ግን ወደዚያ ወርቅ የሚያደርሰን በረሃ (የየዕለቱ ልምምድ፣ የጆርናል ምዝገባ፣ ስቶፕ ሎስን በጸጋ መቀበል እና ራስን መግዛት) እኛን የሚሰራን እውነተኛው ትምህርት ቤት ነው።

በረሃውን አትጥሉት፤ ፈተናውንም አትፍሩት። እያንዳንዱ የቻርት ላይ ፈተና ውስጣችሁ ያለውን "እርሳስ" ወደ "ወርቅ" እየቀየረው ነው!

መልካም የንባብና የትሬዲንግ ሳምንት!

​✍️ ነጋድራስ መሳፍንት

የነጋድራስ አእምሮ | ለአሸናፊ ትሬደሮች የሚሆን የአመለካከት ከፍታ! 07-03-2019 ዓ.ም

Discussion (0)

Be the first to share your read on this.

Log in to join the discussion